• ማሕደረ ዜና

  • Auteur(s): DW
  • Podcast

ማሕደረ ዜና

Auteur(s): DW
  • Résumé

  • ማሕደረ ዜና፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላዉ ዓለም የተደረጉ፣ ሊደረጉ የታቀዱና የተነገሩ ዓበይት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዘወትር ሰኞ ይቃኙበታል። ዝግጅቱ የሐገራትን፣ የዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ማሕበራትን፣ድርጅቶችንና የታዋቂ ግለሰቦችን ያለፈ፣ያሁንና የወደፊት ምግባሮችን እያነሳ በባለሙያዎች አስተያየት የተደገፈ ትንታኔ ይቀርብበታል። አዘጋጅ፣ ነጋሽ መሐመድ
    2025 DW
    Voir plus Voir moins
Épisodes
  • ማሕደረ ዜና፣ የኢራን-አሜሪካ ድርድር ጠብ-ግጭቱን ያበርድ ይሆን?
    Apr 14 2025
    የሙጃህዲያን ኢ-ኻሊቅ (MEK)ና የቡድኑ ምክር ቤት መሪዎች ኢራን በ1967 ከአሜሪካ ባገኘችዉ ድጋፍ የጀመረችዉን የኑክሌር መርሐ ግብርን ወደ ኑክሌር ቦምብ መስሪያነት ለመቀየር ናታንዝና አራክ ዉስጥ በድብቅ እያብላላች መሆኑን ለዓለም አረዱ።ወይም አበሰሩ።ነሐሴ 2003።ዋሽግተን።ሲሞን ሔርሽና ኮኒ ብሩክ የተባሉት መርማሪ ጋዜጠኞች እንደፀፋት የሙጃህዲያን ኢ-ኻሊቅ መሪዎች የቴሕራኖችን ሚስጥር እንዲያጋልጡ የገፋፏችዉ መረጃዉንም የሰጧቸዉ የእስራኤል ባለሥልጣናት ናቸዉ።
    Voir plus Voir moins
    15 min
  • ማሕደረ ዜና፣ የአሜሪካና የኢራን ፍጥጫ-የመካከለኛዉ ምሥራቅ ምሥቅልቅል ሌላ ገፅታ
    Apr 7 2025
    የቴሕራን የፖለቲካና የጦር ሹማምንት ደግሞ ለፕሬዝደንት ትራምፕ ዛቻ አፀፋ ዛቻ እየሰነዘሩ ነዉ።የአያቶላሕ ዓሊ ኻማኒይ የቅርብ አማካሪ አሊ ላርጃኒ ባለፈዉ ሳምንት እንዳሉት ኢራን የኑክሌር ቦምብ መታጠቅ አትፈልግም።የአሜሪካኖች ዛቻ ከበረታ ግን ቀጠሉ የቀድሞዉ የኢራን የኑክሌር ጉዳይ ተደራዳሪ «ሌላ ምርጫ የለንም---መታጠቅ እንጂ።»
    Voir plus Voir moins
    14 min
  • ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ ፈርጀ ብዙ ቀዉስ
    Mar 31 2025
    የብርቱካን ተመስገን ትረካ እዉነት-ሐሰትነት ለብዙዎች በጣሙን እሁለት ለተገመሱት ለማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ አስተያየት ሰጪ-ተከታታዮች ማከራከሩን እንደቀጠለ ነበር።ግን እንዲያዉ ለመጠየቅ ያሕል 120 ሚሊዮን የሚሆነዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሐቁን የሚያወጣ አንድ መርማሪ ፖሊስ፣ አንድ መርማሪ የሕግ ባለሙያ፣ አንድ መርማሪ ጋዜጠኛ፣ አንድ የምክር ቤት አጣሪ ኮሚቴ እንዴት አጣ?
    Voir plus Voir moins
    15 min

Ce que les auditeurs disent de ማሕደረ ዜና

Moyenne des évaluations de clients

Évaluations – Cliquez sur les onglets pour changer la source des évaluations.